
ባሕርዳር: ሚያዝያ 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) ለላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት አቀባበል አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ የገቡትን የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት አቀባበል በማድረጌ ታላቅ ክብር ይሰማኛል ብለዋል።
ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በቅኝ ግዛት ያልተገዙ፣ ለአኅጉሩ ነፃነት እና አንድነት ድምፅ በመኾን ከጋራ የጽናት ታሪክ የሚመነጭ ጥልቅ እና ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት አላቸው። ዛሬም እንደ ሁልጊዜው ኢትዮጵያ ከሰፊ ገበታዋ ያላትን ታላቅ ዐቅምና ዘላቂ ወዳጅነት፣ አብረዋት ለሚጓዙ ሁሉ ለማካፈል ዝግጁ ናት። በዚህ መንፈስ ይህ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማጠናከር፤ የጋራ ሕልሞቻችንን በማይናወጥ መሠረት እና የመፈጸም ቁርጠኝነት ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚኾን ጽኑ እምነት አለኝ ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
