
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ)ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በተለያዩ ጉዳዮች ባጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) እና የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ከሁለትዮሽ ስብሰባቸው ቀጥሎ ሁለት የመግባቢያ ስምምነቶች ልውውጥ ላይ ተገኝተዋል።
እነዚህ ስምምነቶች በትምህርት፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ በማተኮር ለወደፊት ትብብር እንደ ስትራቴጂካዊ መሠረት እና ተግባራዊ ፍኖተ ካርታ ያገለግላሉ ተብሏል።
የትብብር ማዕቀፉ፤ ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያን በመደመር መርሕ በማጣመር ለአኅጉራዊ ትስስር ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ይኾናሉ። የአፍሪካ ሀገራት በእውነተኛ ትብብር ምን ሊያሳኩ እንደሚችሉ እንደ ታላቅ ተምሳሌት የሚጠቀስ ይኾናል ተብሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
