
ባሕርዳር: ሚያዝያ 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) ከላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከላይቤሪያ አቻዬ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ጋር ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
በውይይታችን በተለያዩ ዘርፎች ያለንን የቆየ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለማስፋት ወሳኝ ምዕራፍን ከፍቷል። ከሁለትዮሽ ስብሰባው በመቀጠል፣ በሁለቱ ሀገራት በኩል ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለማሳካት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጡ የመግባቢያ ስምምነቶች እንዲፈረሙ አድርገናል ነው ያሉት።
እነዚህ ስምምነቶች ኢትዮጵያ በፈጣን የለውጥ ጉዞ ያካበተችውን ልምድ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማካፈል፤ ከአጋሮቻችን የተለያዩ ዕይታዎችን በመቅሰም ለአኅጉሩ ዕድገት ዘላቂና አፍሪካዊ መፍትሔዎችን በጋራ ለማፍለቅ እንደ ወሳኝ መሠረት ያገለግላሉ ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
