ለቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

11
አዲስ አበባ: ሚያዝያ 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “የዲጅታል ክህሎት ለዘመነ ኢኮኖሚ” በሚል መሪ መልዕክት ለሥልጠና አስፈላጊ የኾኑ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።
ከዚህ ቀደም በተለያዩ ፕሮጀክቶች አማካኝነት ለበርካታ የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች እና ተቋማት ድጋፍ ሲደረግላቸው መቆየቱን በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የፕሮጀክቶች አስተባባሪ ፕሮፌሰር ሀብቶም ገብረ እግዚአብሔር ተናግረዋል።
የግብርና ኮሌጆችን ጨምሮ ለሌሎችም የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት የአይሲቲ መሠረተ ልማታቸውን ማዘመን የሚያስችል የቁሳቁስ ድጋፎች ርክክብ ተደርጓል ብለዋል አስተባባሪው።
በሀገሪቱ ከ160 በላይ የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ያሉ መኾኑን የገለጹት አስተባባሪው ድጋፉ ለ12ቱ ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አሥተዳደሮች መሰጠቱ ተጠቁሟል።
ዘጋቢ፦ ድልነሳ መንግሥቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleፈተናዎችን በመሻገር ከዕቅድ በላይ ገቢ ለመሠብሠብ እየተሠራ ነው።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) ከላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ጋር ተወያዩ።