ፈተናዎችን በመሻገር ከዕቅድ በላይ ገቢ ለመሠብሠብ እየተሠራ ነው።

8
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአፋር ክልል ገቢዎች ቢሮ መሪዎች በባሕር ዳር ከተማ ተገኝተው ከአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ጋር የገቢ አሠባሠብ የልምድ ልውውጥ አካሄደዋል።
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) ፈተናዎችን በመሻገር ከዕቅድ በላይ ገቢ ለመሠብሠብ እየተሠራ ነው ብለዋል። የግብር ገቢ አሠባሠብ ዘርፍን በማዘመን እና የተለያዩ አማጮችን በመዘርጋት የተሻለ ገቢ እየተሠበሠበ ነው ብለዋል።
በዚህም በመደበኛ ገቢ 66 በመቶ በከተማ አገልግሎት ደግሞ 48 በመቶ ገቢ መሠብሠቡን ተናግረዋል። ልምድ ልውውጡ የተሻለ ለመሥራት እና ግንኙነትን ለማጠናከር ያግዛል ነው ያሉት።
የአፋር ክልል ገቢዎች ቢሮ ኀላፊ ሐጅ አወል ዐብዱ ከክልሉ ስምንት ከተማ አሥተዳደሮች እና ከሰባት ዞኖች ያማከለ ልዑክ ቡድን የገቢ አሠባሠብ ዙሪያ ልምድ ለመለዋወጥ መምጣታቸውን ገልጸዋል። በተለይ የገቢ አሠባሠብ የሕግ ማዕቀፎች አተገባበር ዙሪያ የተሻለ ልምድ መቅሰማቸውንም ነው ያነሱት።
ከሕግ፣ ከአዋጅ እና ከቴክኖሎጂ አንፃር ያሉትን ክፍተቶች ለመሙላት የልምድ ልውውጡ እንደሚያግዝም ተናግረዋል።
የክልሉ የገቢ አሠባሠብ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እንደኾነም ጠቁመዋል።
ይህን የበለጠ ለማሳደግም የልምድ ልውውጡ ድርሻው ከፍተኛ መኾኑን ነው ያነሱት። የገቢ አሠባሠብ ሥራችን በትኩረት ልናከናውነው የሚገባ ሥራ ነው ብለዋል። የልምድ ልውውጡ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩንም ያጠናክራል ነው ያሉት።
የአፋር እና የአማራ ክልል ሕዝብ ተጋምዶ የኖረ ነው፤ ግንኙነቱ ከአመራር ባለፈ በንግድ ዘርፍም ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንደሚሠሩ የተናገሩት ደግሞ የሠመራ ሎጊያ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ዓብዱ ሙሳ ናቸው።
የልምድ ልውውጡ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ እና አንድነትን ለማጠርከር ድርሻው የጎላ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መከሩ።
Next articleለቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።