ለከተሞቻችን ተጨማሪ ውበት እና ምቹነትን እያላበሰ የሚገኘው የኮሪደር ልማት

15

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ አማካሪ ሽቤ ክንዴ ከአሚኮ ወቅታዊ ዝግጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት የኮሪደር ልማት በኹሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች በስፋት እየተተገበረ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

🏙 የኮሪደር ልማት ተደራሽነት

🔹 በ8 ሪጅኦ ፖሊታንት ከተሞች እና በ32 አነስተኛ እና መካከለኛ የክልሉ ከተሞች በስፋት እየተተገበረ መኾኑን ጠቁመዋል።

✍️ የኮሪደር ልማት ክልላዊ እቅድ እና ክንውን

👀 በከተሞች ሽፋን

👉 በ105 ሄክታር በኮሪደር ልማት ተደራሽ ለማድረግ እቅድ ተይዟል። 80 ሄክታር የሚኾነው በመሠራት ላይ መኾኑንም ገልጸዋል።

👀 በመንገድ ልማት

👉 ዋናውን የአስፋልት መንገድ፣ የሳይክል እና የእግረኛ መንገድ ያጠቃለለ 184 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት ለመሥራት ታቅዷል።108 ኪሎ ሜትር (የእቅዱ 60 በመቶ) የሚኾነው በመሠራት ላይ መኾኑንም ተናግረዋል።

🏙 የኮሪደር ልማት በተከናወነባቸው ከተሞች የመጣው ተጨባጭ እምርታ

በክልሉ ከተሞች እየተሠራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት መኾኑን አማካሪው አብራርተዋል።

👉በማኅበረሰቡ ዘንድ ሰፊ የልማት ንቅናቄ እየፈጠረም ነው ብለዋል። የሥራ ባሕል እንዲቀየር ዕድል ፈጥሯልም ነው ያሉት።

👉 የኮሪደር ልማት የከተሞችን ገጽታ ቀይሯል። ከተሞች ጽዱ እና ውብ እየኾኑ ነው።

👉 ከተሞችን ከቁዘማ ወደ ኢኮኖሚያዊ መነቃቃት እያሸጋገረም ይገኛል። የከተማ ቱሪዝም እንዲስፋፋ እያደረገ ስለመኾኑም ተብራርቷል።

👉 በከተሞች ኑሮ እና ሥራ ተጣጥመው እንዲሄዱ ከማድረጉም በተጨማሪ ለነዋሪው ምቹ የሥራ እና የመኖሪያ ከባቢን ፈጥሯል።

👉 ከተሞች ጽዱ እና ውብ ኾነው ሰው ከቦታ ቦታ እንደልብ እንዲንቀሳቀስባቸው አስችሏል። ከጤና አኳያም በተለያዬ መንገድ ለማኅበረሰቡ ከፍተኛ ጠቀሜታን እየሰጠ ይገኛል።

🛣 በኮሪደር ልማት የሚሠሩ ዋና ዋና ተግባራት

👉 የመንገድ – የዋና አስፋልት፣ የሳይክል መንገድ እና እግረኛ መንገድ በኮሪደር ልማት ተካትቶ ይተገበራል።

👉 የአረንጓዴ ልማት- መንገዶችን በአረንጓዴ እጽዋቶች የማስዋብ ሥራም የኮሪደር ልማቱ ዋና አካል ነው።

👉 የሕዝብ አገልግሎት ሰጭዎች-አደባባዮች ፓርኮች 🏝 ፣ ካፍቴሪያዎች 🏡፣ መጸዳጃ ቤቶች እና ሌሎችም ከኮሪደር ልማቱ ጋር የሚተገበሩ ናቸው ብለዋል።

👉 የተቀናጀ መሠረተ ልማት – ኮሪደር ልማቱን ዘላቂ ለማድረግ ከመብራት፣ ውኃ እና የቴሌ ኮሚዩኒኬሽን መሥመሮችን አብሮ የመዘርጋት ሥራ በቅንጅት መሥራት የኮሪደር ልማቱ አካል ተደርጎ እየተሠራ ይገኛል።

👉 ከተሞችን ለስማርት ከተማ ምቹ የማድረግ – 🚏 ስማርት ፖሎች እና የደኅንነት ካሜራዎችን 📷 የመትከል ሥራም አብሮ እየተሠራ ነው።

የኮሪደር ልማት ትኩረት መንገድን ብቻ ሳይኾን ስማርት ሲቲ ሊያሟላቸው የሚገቡ ኹሉንም ነገሮች ዘላቂ በመኾነ መንገድ የሚተገበርበት መኾኑን አቶ ሽቤ ገልጸዋል።

ዘጋቢ፦አድኖ ማርቆስ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleድህነት ለሉዓላዊነት መሸርሸር ዋና መንስኤ ነው።
Next articleሰላምን እያረጋገጡ አስፈላጊውን ገቢ መሠብሠብ እና ልማትን መሥራት ያስፈልጋል።