
በምክክር መፍትሔ በመሻት ከግጭት አዙሪት መውጣት እና ለዜጎቿ ሁሉ የምትመች ጠንካራ ሀገር በጋራ መገንባት እንደሚገባ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴሃን) ሊቀመንበር ተስፋሁን ዓለምነህ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ በብሔራዊ ጥቅም፤ በሀገራዊ አንድነት እና በሰላም ግንባታ ዙሪያ አዴሃን የማይናወጥ አቋም በመያዝ የሚሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በርካታ ሂደቶችን አልፎ የምክክር ጉባኤው የሚካሄድበት ዋዜማ ላይ ይገኛል። ነገ ሐምሌ 08/2018ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል።
የምክክሩ ሂደት እስካሁን በጥሩ ስኬት መዝለቁንም አንስተዋል። ኢዜአ እንደዘገበው የመጨረሻው ውጤትም የተሳካ እንዲኾን የሁላችንም ዝግጁነት እና ቀና ትብብር ያስፈልጋል ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
