ቤጂንግ የሻከረውን የአሜሪካ እና ኢራን ግንኙነት በማርገብ በቀጣናው ሰላም እንዲሰፍን ያላሰለሰ የዲፕሎማሲ ጥረት እንደምታደርግ ገለጸች።

9
🚢
አሜሪካ እና ኢራን በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ በኩል አስተማማኝ የጉዞ መስመርን በፍጥነት እንዲመልሱ ቻይና ጠይቃለች።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የቆየ የፖለቲካ ውጥረት አሁንም እንደቀጠለ ነው። በተለይም ይህ ስትራቴጂካዊ የውኃ መስመር እንዴት መተዳደር አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ አለመግባባቶች ዳግም አገርሽተዋል።
በአሁኑ ወቅት አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው ማዕቀብ እና የኢራን የኒውክሌር መርሐግብር የሁለቱ ሀገራት ዋነኛ የልዩነት መንስኤዎች ኾነው ቀጥለዋል።
በተጨማሪም በመካከለኛው ምሥራቅ በሚታየው የውክልና ግጭት ምክንያት የባሕር ላይ ደኅንነት ክፉኛ ተጓድሏል።
የንግድ መርከቦች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እና መስተጓጎሎች በዓለም አቀፉ የነዳጅ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅነዋል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን በሰጡት መግለጫ ይህንኑ የጸጥታ ስጋት አንስተዋል።
በወሽመጡ መደበኛ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንግድ ትራንስፖርትን ማስቀጠል የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የጋራ ፍላጎት መኾኑንም አብራርተዋል።
ቤጂንግ ይህንን የሻከረ ግንኙነት በማርገብ በቀጣናው ሰላም እንዲሰፍን ያላሰለሰ የዲፕሎማሲ ጥረት እንደምታደርግም አረጋግጠዋል።
በስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleበፈተና ውስጥ የተዘራ የዕድገት ዘር እና የሰላም ጥም
Next articleበምክክር ከግጭት አዙሪት መውጣት እና ጠንካራ ሀገር መገንባት አለብን።