ድህነት ለሉዓላዊነት መሸርሸር ዋና መንስኤ ነው።

11

 

አዲስ አበባ: ሚያዝያ 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የፓናል ውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው። የፓናል ውይይቱ “ከተረጅነት ወደ ምርታማነት” በሚል መሪ መልዕክት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በፓናል ውይይቱ ላይ ተገኝተው ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ.ር) የመሪ እና የማኅበረሰቡን የሥራ ባሕል ማሳደግ እንደሚገባ አንስተዋል።

ተነሳሽነትን በማሳደግ ተረጅነትን እና ልመናን ታሪክ ማድረግ እንደሚቻልም ገልጸዋል።

በተለይም እንደ ሀገር ያለንን ፀጋ እና የመሥራት አቅምን በተገቢው መንገድ በመለየት ከድህነት ማነቆ መውጣት ይገባናል ብለዋል።

ድህነት ለሉዓላዊነት መሸርሸር ዋና መንስኤ መኾኑንም ገልጸዋል።

የግብርና ሚኒስትር ድኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ.ር) ከተረጅነት እና ከልመና ለመውጣት የአካባቢ ጸጋን አሟጦ መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።

ከተረጅነት እና ከልመና ለመውጣት የሚያስችል ብዙ አማራጭ እንዳለም ጠቁመዋል።

ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን እና የቱሪዝም ዘርፉን በማስፋት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ነው ያሉት።

በቆራጥነት ከድህነት፣ ከኋላቀርነት እና ከልመና አስተሳሰብ ለመውጣት ቆርጠን መነሳት አለብን ብለዋል።

ግብዓቶችን እና ቴክኖሎጂዎችን በማቀናጀት ድህነትን ታሪክ ማድረግ የዚህ ትውልድ ቀዳሚ ኀላፊነቱ መኾኑንም ተናግረዋል።

ልመና እና የተረጅነት አስተሳሰብን ከራሳችን አራግፈን በመጣል የጀመርነውን ለውጥ አጠናክረን እንቀጥላለንም ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ሰለሞን አሰፌ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሀሰተኛ የምስሎችን እንዴት እንለይ?
Next articleለከተሞቻችን ተጨማሪ ውበት እና ምቹነትን እያላበሰ የሚገኘው የኮሪደር ልማት