ሀሰተኛ የምስሎችን እንዴት እንለይ?

6
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ)
✍️ ጉግል ሪቨርስ ኢሚጅ ሰርችን በመጠቀም፦ ለማረጋገጥ ያስገባንለትን ምስል እጅግ ብዙ ከኾኑ የሳይበር ዓለም ምስሎች ጋር በማነጻጸር ተያያዥ፣ የተቀየጡ እና ራሱን ያስገባነውን ምስል ጨምሮ ያመጣልናል። ምስሉን ለመፈለግ ነጥቦችን፣ መስመሮችን፣ ቀለሞችን እና ቴክስቼሮችን በጥልቀት ያጤናል።
✍️ቲን አይን በመጠቀም፦ እንዲፈለግ የተሰጠውን ምስል በመጀመሪያ መለያ ይፈጥርለት እና ለዚያ መለያ የሚገጥም ሌላ ምስል ይፈልጋል። የፍለጋ ውጤቱ ራሱን የተፈለገውን ምስል፣ በዋናው ምስል ላይ ለውጥ ከተደረገ ያን የተለወጠ ምስል እና ከዋናው ምስል ላይ የመጠን ለውጥ ተደርጎበት ከኾነም ያንኑ ያመጣልናል።
✍️ ፎቶ ፎሬንሲክን በመጠቀም፦ የሰው ዐይን ሊያስተውለው የማይችለውን ይዘት በጥልቅ ምልከታ በመመርመር ለመለየት ያስችላል። በተለየ ኹኔታ ምስሉ የተቀረጸበትን መሳሪያ ሞዴል፣ ቦታ እና የተጨመረ ቅንብርን ይለያል።
የቴክኖሎጂ እድገት እና የመረጃ ተለዋዋጭነት ካለው ፍጥነት አንጻር በሳይበር ዓለም የሚገኙ ይዘቶችን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ከጊዜው ጋር የሚሄድ ተግባር ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበነጻ የንግድ ቀጠና ውስጥ ተሰማርተው ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርቡ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተፈቀደ።
Next articleድህነት ለሉዓላዊነት መሸርሸር ዋና መንስኤ ነው።