የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ 3ኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬም መደረጋቸውን ይቀጥላሉ።

0
136
ዛሬ 9 መርሀግብሮች የሚከናወኑ ሲሆን ባየርሙኒክ አርሰናልን የሚገጥምበት ትኩረት ሳቢ ነው። በአልያንዝ አሬና አስፈሪ ማጥቃት ያለው ባየርሙኒክ የተደራጀ መከላከል ያለውን አርሰናልን ያስተናግዳል።
አርሰናል ሁለቱንም የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ሲያሸንፍ ግብ አልተቆጠረበትም። ሙኒክ ደግሞ በሻምፒዮንስ ሊጉ ከሚገባው 6 ነጥብ 4 ብቻ ቢያሳካም ከሰሞኑ ሊፕዚሽን በቦንደስሊጋው 6ለ1 ያሸነፈበትን ጨምሮ አስፈሪ ማጥቃት አለው።
ለምሽት 4:00 ጨዋታ በሙኒክ በኩል አማካኙ ጆሽዋ ኪሚክ በቤተሰብ ጉዳይ የመስመር አጥቂው ኦሊሴ በቅጣት አይሰለፉም። በአርሰናል በኩል አዲስ የጉዳት ዜና የለም።
ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም በአውሮፓ መድረክ 15 ጊዜ ተገናኝተው ባየር ሙኒክ 8 ለ4 የማሸነፍ የበላይነት አለው። በሌሎች ጨዋታዎች የውድድሩ ስኬታማ ክለብ ሪያል ማድሪድ የጀርመኑን ሊፕዚሽ ያስተናግዳል።
👉 አስቶንቪላ ከ ቫይኪንግ
👉ክለብ ብሩጅ ከ ሌንስ
👉ኢንተር ሚላን ከ ሻክታር ዶኔስክ
👉 ሪያል ቤትስ ከፌኖርድ
👉ስፓርቲንግ ከ ላስክ በሙሉ ጨዋታቸውን ምሽት 4:00 ሲጀምሩ
👉ሊል ከጋላታሳራይ እና ኮሞ ከማንችስተር ዩናይትድ ቀደም ብለው ምሽት 1:45 ጨዋታቸውን ይጀምራሉ።
መለሰ ግዛቸው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here