የዳካር 2026 ወጣቶች ኦሎምፒክ የቴኳንዶ ውድድር ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 4 ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል። ወጣት የቴኳንዶ ስፓርት ተወዳዳሪዎች በወንዶችና በሴቶች ምድቦች የሚወዳደሩ ሲሆን፣ በተጨማሪም የድብልቅ ውድድርም የዚሁ አካል እንደሆነ መርሃግብሩ ያሳያል።ሀገራት እንደተፈቀደላቸው የኮታ መጠን ተወዳዳሪዎችን የሚያሰልፉ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም በዚሁ ውድድር በወንዶች ከ 48 ኪሎ ግራም በታች ተሳታፊ ትሆናለች።ከ99 ተሳታፊዎች መካከል ኢትዮጵያን በብቸኝነት የሚወክለው ደግሞ ሲፈን ታዬ ነው።ተወዳዳሪው ሲፈን ታዬ ለውድድሩ ብቁና ዝግጁ ለመሆን በደቡብ ኮሪያ ሙጁ (Muju) በተካሄደው “WT-Olympic Solidarity Targeted Training Camp” የተሰኘ ከፍተኛ የስልጠና ካምፕ ላይ ተሳትፎ ስልጠናውን አጠናቋል። ይህን የአትሌቱን የስልጠናና የዝግጅት ሂደት በዋና አሰልጣኝነት የመሩት ማስተር አዲሱ ኡርጌሳ ናቸው።ይህ በዓለም አቀፍ የቴኳንዶ ፌዴሬሽን (WTF) እና በኦሎምፒክ ሶሊዳሪቲ አዘጋጅነት የተሰጠው ስልጠና አትሌቱ በዳካር ኦሎምፒክ ለሚያደርገው ውድድር በቴክኒክ፣ በታክቲክ እና በአካላዊ ብቃት በኩል ከፍተኛ ዝግጅት እንዲያደርግ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል።ስልጠናዉ ከመስከረም 18 እስከ መስከረም 28 ቀን 2019 ድረስ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ11 ሀገራት የተወጣጡ 20 ወጣት ስፖርተኞች እና 12 አሰልጣኞች ተሳትፈውበት ነበር።በወንዶችና በሴቶች አምስት አምስት የመወዳደሪያ የክብደት መጠኖች ያሉ ሲሆን በወንዶች ዘርፍ ከ 48ኪ.ግ በታች ፣ ከ55ኪ.ግ በታች ፣ በ63ኪ.ግ፣ ከ73ኪ.ግ በታችና እና ከ73ኪ.ግ በላይ ይወዳደራሉ።በሴቶች ዘርፍ ደግሞ ከ44ኪ.ግ በታች ፣ ከ49ኪ.ግ በታች፣ ከ55 ኪ.ግ በታች፣ ከ63 ኪ.ግ በታች እና ከ63ኪ.ግ በላይ ዘርፎች ለሜዳልያ ይፎካከራሉ።በተጨማሪም የወንዶችና የሴቶች ድብልቅ ውድድር ተካቶ ይካሄዳል።በዚህ ታሪካዊ የዳካር ወጣቶች ኦሎምፒክ የቴኳንዶ ውድድር ላይ ከ66 በላይ ሀገራት የተወጣጡ 99 ስፓርተኞች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሐናማርያም መስፍን
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_28_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



