አንዱ የሌላውን መሸነፍ የሚናፍቅበት የአርሰናል እና የማንቸስተር ሲቲ ጨዋታዎች በተለያዩ ሜዳዎች።

0
15

በአሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመራው እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መሪው አርሰናል በ10ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኸል ሲቲን በኤሚሬትስ ስታዲየም ከምሽቱ 12፡00 ላይ ያስተናግዳል።የሊጉ መሪ እና ከባድ የሜዳ ውጭ ጨዋታዎች በብቃት ያጠናቀቀው አርሰናል፣ በሳምንቱ አጋማሽ በሻምፒዮንስ ሊጉ ስላቪያ ፕራግን 2 ለ 1 በማሸነፍ በጥሩ አቋም ላይ ይገኛል።ቡድኑ አሁን ላይ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት ነው ዛሬ የሚጫወተው።ከ10 ዓመታት በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የተመለሰው ኸል ሲቲ ለታላላቅ ክለቦች ፈታኝነቱ የሚታወቅ በመኾኑ አርሰናል ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ጨዋታውን እንደሚያደርግ ይጠበቃል።በአርሰናል በኩል በጉዳት ምክንያት ከሜዳ ርቆ የነበረው ተከላካዩ ዊሊያም ሳሊባ ወደ ሥብሥቡ ተመልሷል። ኾኖም ቡካዮ ሳካ በጉዳት እንዲሁም ወጣቱ ማክስ ዳውማን በቅጣት ምክንያት በጨዋታው ላይ አይሰለፉም። ተከላካዩ ኤዝሪ ኮንሳም በጨዋታው የመሰለፉ ነገር አጠራጣሪ እንደኾነ ተገልጿል።በሌላ በኩል ኖቲንግሃም ፎረስት ማንቸስተር ሲቲን የሚጋብዝበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።ማንቸስተር ሲቲ በቻምፒየንስ ሊግ አርቢ ላይፕዚግን 3 ለ 2 ካሸነፈ በኋላ በፕሪሚየር ሊጉ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ጨዋታ ያደርጋል።በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም ከምሽቱ 2:30 ላይ በሚካሄደው በዚህ ጨዋታ ሲቲ በፕሪምየር ሊጉ ያለውን ተፎካካሪነት ለማስጠበቅ ትኩረት ሰጥቶ የሚጫዎት በመኾኑ ነው ተጠባቂ ያደረገው።ፎረስት በውድድር ዘመኑ አንድ ጨዋታ ብቻ በማሸነፍ እና አንድ አቻ በመለያየት ቀሪዎቹን ደግሞ በሽንፈት በማጠናቀቅ በወራጅ ቀጣናው በሰንጠረዡ ግርጌ አንድ ከፍ ብሎ ይገኛል።ማንቸስተር ሲቲ ደግሞ በሊጉ ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች የተሸነፈ በመኾኑ ከድል ጋር ለመታረቅ ወደ ሜዳ ይገባል።በማንቸስተር ሲቲ በኩል አንቶኒ ሴሜንዮ በጉዳት ምክንያት የማይሰለፍ ብቸኛው ተጫዋች ነው።በኖቲንግሃም ፎረስት በኩል ደግሞ ኒኮሎ ሳቮና፣ ኒኮላስ ዶሚንጌዝ እና ኢጎር ጂሰስ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጪ ናቸው።ሁለቱ ቡድኖች በታሪካቸው 109 ጊዜ የተገናኙ ሲኾን ማንቸስተር ሲቲ 46 ጊዜ ሲያሸንፍ ፎረስት 34 ጊዜ አሸንፏል።ኖቲንግሃም ፎረስት በዚህ የውድድር ዘመን በሜዳው እስካሁን ምንም ግብ አላስተናገደም ዛሬስ የሚለው የሚጠበቅ ነው የሚኾነው።ኤርሊንግ ሀላንድ በዚህ ጨዋታ ግብ ካስቆጠረ በዚህ ጨዋታ በታሪክ ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች በመኾን ከኒያል ኩዊን ጋር ታሪክ ይጋራል። በሌሎች ጨዋታዎች ቀን 9:30 ሊድስ ዩናይትድ ከቶተንሀም ሆትስፐር እንዲሁም ፉልሀም ከኒውካስትል 12:00 ይጫወታሉ።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_28_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here