ዛሬ 9 መርሀግብሮች የሚከናወኑ ሲሆን ባየርሙኒክ አርሰናልን የሚገጥምበት ትኩረት ሳቢ ነው። በአልያንዝ አሬና አስፈሪ ማጥቃት ያለው ባየርሙኒክ የተደራጀ መከላከል ያለውን አርሰናልን ያስተናግዳል።
አርሰናል ሁለቱንም የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ሲያሸንፍ ግብ አልተቆጠረበትም። ሙኒክ ደግሞ በሻምፒዮንስ ሊጉ ከሚገባው 6 ነጥብ 4 ብቻ ቢያሳካም ከሰሞኑ ሊፕዚሽን በቦንደስሊጋው 6ለ1 ያሸነፈበትን ጨምሮ አስፈሪ ማጥቃት አለው።
ለምሽት 4:00 ጨዋታ በሙኒክ በኩል አማካኙ ጆሽዋ ኪሚክ በቤተሰብ ጉዳይ የመስመር አጥቂው ኦሊሴ በቅጣት አይሰለፉም። በአርሰናል በኩል አዲስ የጉዳት ዜና የለም።
ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም በአውሮፓ መድረክ 15 ጊዜ ተገናኝተው ባየር ሙኒክ 8 ለ4 የማሸነፍ የበላይነት አለው። በሌሎች ጨዋታዎች የውድድሩ ስኬታማ ክለብ ሪያል ማድሪድ የጀርመኑን ሊፕዚሽ ያስተናግዳል።
መለሰ ግዛቸው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



