ፓሪሴን ዥርሜን በጉዳት ታምሷል።

0
148
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በባርሴሎና ላይ አስደናቂ ድል ካስመዘገቡ ማግስት በፓርክ ዲ ፕሪንስ ጉዳት በርክቷል።
ቡድኑ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት አጥቂው ኦስማን ደምበሌ እና ተከላካዪ ማርኪንዮስ ጉዳት ገጥሟቸዋል።
ተጨዋቾቹ በቀኝ እግራቸው በተመሳሳይ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠማቸውም ታውቋል። በዚህም ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃሉ።
ከደምበሌና ማርኪንዬስ በተጨማሪ ክቫርስኬልያ እና ኑኖ ሜንዴዝ ጉዳት ያጋጠማቸው የክለቡ ተጨዋቾች ናቸው።
በተለይ የኪቪቻ ክቫርስኬልያ ጉዳት ቀዶ ጥገና የሚያስፈልገው በመሆኑ ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ይርቃል።
መለሰ ግዛቸው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here