የባርሴሎና የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች የሆነው ራፊኒያ ትላንት ምሽት በፒኤስጂ ከደረሰባቸው የ4ለ2 ሽንፈት በኃላ አስተያየቱን የሰጠ ሲሆን ያጣነው ሶስት ነጥብ ብቻ ነው በማለት ተናግሯል።
ትላንት ምሽት በፒኤስጂ እና ባርሴሎና መካከል በተደረገው የሶስተኛ ዙር የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ሽንፈት የደረሰባቸው ብሉ ግራናዎቹ በውድድር አመቱ የመጀመሪያ ሽንፈታቸውን በፓርክ ደ ፍራንስ አስተናግደዋል ።
ከምሽቱ ሽንፈት በኃላ ሀሳቡን የገለፀው ብራዚላዊው ተጨዋች ራፊኒያ የተጫወትነው ባለፉት ሁለት አመታት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግን ካሸነፈ ክለብ ጋር ነው ስለዚህ ምንም ሚያስደንቅ ነገር የለም። ከፒ ኤስ ጅ ጋር በሜዳቸው ወጫዎት ከባድ ነው። በቀጣይ ጨዋታዎች ተሻሽለን እንመጣለን በማለት ተናግሯል ።
እቅዳችን አሸንፎ መመለስ ቢሆንም አልተሳካም ። ግን ትልቅ ጉዳይ አይደለም ያጣነው 3 ነጥብ ነውና ሲልም የባርሳው አምበል ገልጿል።
በዚህ ጨዋታ መሸነፋቸው በኤልክላሲኮ ደርቪ ከማድሪድ ጋር ያለባቸው ዝግጅት ላይ ተፅእኖ እንደሌለውም አስረድቷል ። ያሆ ስፓርት
እንዳስነበበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



