የኢትዮጱያ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት መርሃግብር ዛሬ 4 ጨዋታዎች ይካሄዳሉ፡፡

0
115
ወላይታ ዲቻ ከባህር ዳር ከተማ የሚያደርጉት የሃላባ ስታዲየም ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ ዲቻ በውድድር አመቱ ከድል ጋር ለመገናኘት የጣና ሞገዶቹ ደግሞ ወደ ድል ለመመለስ ይፋጠጣሉ፡፡
ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም 14 ጊዜ ተገናኝተው ባህር ዳር ከተማ 4ለ2 የማሸነፍ የበላይነት አለው፡፡ 8 ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል፡፡
በተመሳሳይ ሰአት ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ አበባ ላይ አዳማ ከተማን ሲያስተናግድ በሸገር ደርቪ ከደረሰበት የሽንፈት ስነልቦና ለመላቀቅ በማሰብ ነው፡፡ ቡድኑ ዘንድሮ ከድል ጋር አልተገናኘም፡፡
በቡድኖች ግንኙነት ታሪክ ፈረሰኞች 25ለ10 የማሸነፍ ሃያልነት አላቸው፡፡ በተመሳሳይ ሰአት ሃዋሳ ንግድ ባንክን ያስተናግዳል፡፡ በተቃርኖ ውጤት ላይ የሚገኙ ቡድኖች ጨዋታ ነው፡፡ ባንክ ሁለቱንም ጨዋታዎች ያሸነፈ ብቸኝ ቡድን ነው፡፡ ሃዋሳ ደግሞ ከድል ጋር አልተገናኘም፡፡
10፡00 ላይ አዲስ አዳጊው ጋሞ ጨንታ መቻልን ይገጥማል፡፡ ጋሞ ጨንታ የፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ጨዋታው ሲሆን የመጀመሪያ ነጥቡን ለማግኘጥ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡
መቻል ደግሞ ከንግድ ባንክ ሽንፈቱ ወደ ድል ለመመለስ ይታትራል፡፡ ጨዋታው በአርባምንጭ ስታየም ይደረጋል፡፡
መለሰ ግዛቸው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here