“እኛ ትኩረታችን ከሊቨርፑል ጋር በምናደርገው ጨዋታ ላይ ነው” የሲቲው አሠልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ

0
22
ኤንዞ ማሬስካ በማንችስተር ሲቲ ላይ የተሰጠውን የጥፋተኝነት ውሳኔ አጣጣሉ፤ ትኩረታቸው በሜዳ ላይ ተግባር ላይ መኾኑንም ገለጹ።
የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ክለባቸው በፕሪሚየር ሊጉ የፋይናንስ ሕግጋት መጣስ ጥፋተኛ ተብሎ ከተበየነበት ውሳኔ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየት የሰጡ ሲኾን፣ እሳቸውም ኾኑ ተጫዋቾቻቸው በውሳኔው አለመጨነቃቸውን እና ሙሉ ትኩረታቸው በሜዳ ላይ እግር ኳስ አፈጻጸም ላይ መኾኑን ገልጸዋል።
ማንችስተር ሲቲ ከ2009 እስከ 2018 ባሉት ዓመታት ውስጥ የገቢ መጠንን አጋኖ ለማሳየት እና ወጪዎችን ለመቀነስ ሕገ-ወጥ የንግድ ውሎችን ተጠቅሟል በሚል በነጻ አቅራቢ ኮሚሽን ጥፋተኛ ተብሏል። ይህም ከባድ የነጥብ ቅነሳ ወይም ከሊጉ እስከ መሰረዝ የሚደርስ ቅጣት ሊያስከትልበት የሚችል ቢኾንም ክለቡ በውሳኔው ላይ ይግባኝ ብሏል።
አሰልጣኙ ኤንዞ ማሬስካ ታዲያ ለክለቡ ሚዲያ በሰጡት መግለጫ «እኔ በጣም በክለቡ እተማመናለው፤ ክለቡም ቢኾን ግልጽ ምላሽ ሰጥቷል።
በክለባችን ሙሉ በሙሉ እንተማመናለን። የውጭውን ድምጽ እና ወሬ እንረዳዋለን፤ ነገር ግን የእኛ ትኩረት መቆጣጠር በሚቻለው በሜዳ ላይ እግር ኳስ ላይ ብቻ ነው» ብለዋል።
ተጫዋቾቹ ከብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ከተመለሱ በኋላ ባደረጉት ልምምድ ስለ ጉዳዩ የተነጋገሩ ሲኾን፣ ማሬስካ እንደገለጹት ተጫዋቾቹ በወሬው ሳይበገሩ በሜዳ ላይ ውጤታማነታቸው ላይ ብቻ ትኩረት አድርገዋል።
በአሁኑ ወቅት በሊጉ ያደረጓቸውን አምስቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ የደረጃ ሰንጠረዡን በበላይነት የሚመሩት ማንችስተር ሲቲዎች፣ እሑድ ዕለት ከአንፊልድ ከሊቨርፑል ጋር ከባድ ፍልሚያ የሚያደርጉ ሲኾን፣ ረቡዕ ደግሞ በቻምፒዮንስ ሊግ የፓሪስ ሴንት ዠርሜን እንግዳ ይኾናሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here