በውዝግብ የተሞላው የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ከተካሄደ ከዘጠኝ ወራት በኋላ ሴኔጋል እና ሞሮኮ በዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (ሲኤኤስ) የሕግ ክርክር ላይ ይገኛሉ።
ፍርድ ቤቱ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ሞሮኮ ያገኘችው የ 3 ለ 0 አሸናፊነት እንዲጸና ይደረግ ወይም አይደረግ በሚለው ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በጨዋታው ማጠናቀቂያ ክፍለ ጊዜ ላይ በተሰጠ አወዛጋቢ የፍጹም ቅጣት ምት ምክንያት የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን አባላት ተቃውሟቸውን ገልጸው ከሜዳ በመውጣታቸው፣ የሴኔጋል የሻምፒዮንነት ማዕረግ መነጠቁ ይታወሳል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



