የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ አሠልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ዌይን ሩኒ በኦልድ ትራፎርድ አብረው በነበሩበት ዘመን በአውሮፓ ውስጥ ከነበሩ ተጫዋቾች ሁሉ ምርጦቹ ሁለቱ እንደነበሩ ገልጸዋል።
ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ከስካይ ስፖርት ጋር ባደረጉት ቆይታ «በዚያ ወቅት ሁለቱ ተጫዋቾች በአውሮፓ ውስጥ ከነበሩት ሁሉ ምርጦቹ እንደነበሩ ሙሉ በሙሉ አምናለሁ» ብለዋል።
አሠልጣኙ የሁለቱን ተጫዋቾች ልዩ የሜዳ ላይ ጥምረት ሲያወድሱ «ከሊቨርፑል የመጣው አጭሩ እና ደልዳላው ልጅ ሩኒ እና ከፖርቱጋል የመጣው ረጅሙ ወጣት ሮናልዶ አብረው ያሳዩት ድንቅ የሜዳ ላይ ቅንጅት እና ጥምረት በጣም አስደናቂ ነበር» ሲሉ ተናግረዋል።
ሁለቱ ተጫዋቾች በማንችስተር ዩናይትድ በነበራቸው ስኬታማ ቆይታ ክለቡ የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ጨምሮ በርካታ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን እንዲያሸንፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ይታወሳል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



