“የቬንገር አሸኛኘት በአርሰናል ታሪክ ላይ ጥቁር ነጥብ ነው” ሰር አሌክስ ፈርጉሰን

0
17
የቀድሞው የማንቼስተር ዩናይትድ አሠልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን አርሴን ቬንገር በአርሰናል የመጨረሻዎቹ ዓመታት ከደጋፊዎች የገጠማቸው መጥፎ ተቃውሞ “በክለቡ ታሪክ ላይ የተቀመጠ ጥቁር ነጥብ” ሲሉ ገልጸውታል።
ፈርጉሰን እንዳሉት ቬንገር ለለንደኑ ክለብ ያበረከቱት ታላቅ ውለታ እና ያስመዘገቡት አስደናቂ ውጤት ዋጋ ሊሰጠው የሚገባ እንደነበር ገልጸው በወቅቱ ከደጋፊዎች የደረሰባቸው ጫና ተገቢ አልነበረም ነው ያሉት።
አርሴን ቬንገር ከአርሰናል ጋር 3 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎች ያለ ምንም ሽንፈት የተጠናቀቀውን ታሪካዊ የ2003/04 የውድድር ዘመን ጨምሮ፣ 7 የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫዎችን አሳክተዋል።
ፈረንሳዊው አሠልጣኝ አርሴን ቬንገር አርሰናልን ለ22 ዓመታት በመምራት በክለቡ ታሪክ ከፍተኛውን ስኬት ያስመዘገቡ እና የዘመናዊ እንግሊዝ እግር ኳስ ዕድገት ላይ ትልቅ አሻራ ያሳረፉ አሠልጣኝ እንደኾኑ ይታወቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here