የቱርክ ወጣት የፊት መስመር እና አማካይ ተጫዋች አርዳ ጉለር በመስከረም ወር ያሳየውን ድንቅ አፈጻጸም ተከትሎ የሪያል ማድሪድ የወሩ ኮከብ ተጫዋች ሽልማቱን ተረክቧል።
ወጣቱ ባለተሰጥኦ ተጫዋች በወሩ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ለሪያል ማድሪድ ያበረከተውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እና ያሳየውን የሜዳ ላይ የበላይነት ተከትሎ በደጋፊዎች ድምጽ የወሩ ምርጥ ተጫዋች ኾኖ ተመርጧል።
አርዳ ጉለር የመስከረም ወር ኮከብነቱን የሚያረጋግጠውን ዋንጫ ዛሬ ከተረከበ በኋላ ደስታውን ገልጿል።
የ19 ዓመቱ የቱርክ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች በሳንቲያጎ በርናቤው አዲስ ታሪክ እየጻፈ የሚገኝ ተጫዋች ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



