የአርጀንቲናው አማካኝ ኤንዞ ፈርናንዴዝ ለማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎች ባስተላለፈው መልዕክት ከክለቡ ጋር በመኾን በርካታ ዋንጫዎችን የመቀዳጀት ትልቅ ዓላማ እንዳለው ገልጿል።
ኤንዞ ለተደረገለት የሞቀ አቀባበል ደጋፊዎችን አመስግኖ፣ «በእውነት ክለቡ እንደ ቤቴ ኾኖ ይሰማኛል፤ ይህም ለአንድ ተጫዋች በራስ መተማመን በጣም ወሳኝ ነው» ብሏል።
አያይዞም «ክለቡ በዚህ የውድድር ዘመን ያቀዳቸውን ግቦች ለማሳካት አብረን በርካታ ዋንጫዎችን ለማንሳት እና በጨዋታችን እንድንደሰት በየቀኑ፣ በየልምምዱ እና በየጨዋታው መቶ በመቶ አቅሜን እሰጣለሁ» ሲል ቁርጠኝነቱን አረጋግጧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



