ቻድ እግር ኳሷን ለማሳደግ ከስፔኑ ላሊጋ ጋር ስትራቴጂካዊ ስምምነት ተፈራረመች።

0
25

 

የቻድ የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር ናኢር አባካር እና የላሊጋው ፕሬዚዳንት ሃቪየር ቴባስ በማድሪድ ባደረጉት ስብሰባ የሀገሪቱን እግር ኳስ መዋቅር ለማዘመን ያለመ ስትራቴጂካዊ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

የስምምነቱ ዋና ዓላማ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ልምዶች በመጠቀም የቻድን ብሔራዊ ሊግ በፕሮፌሽናል ደረጃ ማደራጀት፣ የታዳጊ ሥልጠናዎችን ማጠናከር እና አዳዲስ ባለክህሎት ተጫዋቾችን ማፍራት ነው።

ይህ ትብብር ቻድ የስፖርት አቅሟን ለማሳደግ የያዘችውን አቅጣጫ የሚያፋጥን ሲኾን፣ ለአፍሪካ እግር ኳስ ዕድገትም ትልቅ እርምጃ እንደኾነ መገለጹን ስካይ ስፖርት ዘግቧል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_22_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here