በክርስቲያኖ ሮናልዶ እና በፖርቹጋል አሠልጣኝ ሆርሄ ሄሱስ መካከል የነበረው አለመግባባት መፍትሔ አገኘ።

0
77
በፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አንበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና በአሠልጣኙ ሆርሄ ሄሱስ መካከል ተከስቶ የነበረው አለመግባባት በስምምነት መቋጨቱ ተገልጿል።
የፖርቹጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አለመግባባቱን በሰላም ለመፍታት እና በቡድኑ መልበሻ ክፍል ውስጥ መረጋጋትን ለመመለስ ሲሉ በግላቸው ወደ ዴንማርክ በመጓዝ በድርድሩ ላይ ተሳትፈዋል።
አርቲፒ ኖቲሲያስ እንደዘገበው ከኾነ በሁለቱ አካላት መካከል የነበረው ውጥረት መፍትሔ ማግኘቱን ተከትሎ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ሆርሄ ሄሱስ በዛሬው ዕለት በሚሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለሁኔታው ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here