«ከምንጊዜውም በላይ ከክለቤ ጋር ነኝ» ፔፕ ጓርዲዮላ ለሲቲ ደጋፊዎች የጻፉት ደብዳቤ

0
69

 

ማንቸስተር ሲቲ በቀረቡበት የፋይናንስ ደንብ ጥሰት ክሶች ጥፋተኛ ኾኖ መገኘቱን ተከትሎ የማንቼስተር ሲቲ አሠልጣኝ የነበሩት ፔፕ ጓርዲዮላ ለክለቡ ደጋፊዎች በላኩት ግልጽ ደብዳቤ በዚህ ወቅት ከምንጊዜውም በላይ ከክለቡ ጎን መኾናቸውን አረጋግጠዋል።

ፔፕ በመልዕክታቸው «እያንዳንዱ የማንቼስተር ሲቲ ደጋፊ ከምንጊዜውም በላይ ከእናንተ ጋር መኾኔን እንድታውቁ እፈልጋለሁ» ካሉ በኋላ፣ ሁልጊዜም ቢኾን ከክለባቸው፣ ከባለቤቱ፣ ከሊቀመንበሩ፣ ከተጫዋቾች፣ ከአሠልጣኞች ስታፍ እና ከደጋፊዎቻቸው ጎን መኾናቸውን ገልጸዋል።

አሠልጣኙ አክለውም «ይህንን ጊዜ በጋራ እንሻገረዋለን» ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው ያላቸውን ጽኑ አቋም እና ፍቅር ገልጸዋል።

ፔፕ ጋርድዮላ በማንቸስተር ሲቲ የአስር ዓመት ቆይታቸው በርካታ ዋንጫዎችን ወደ ኢቲሃድ ማምጣታቸው ይታወሳል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_20_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here