የኢትዮጵያውያንን የኳስ ፍቅር ለማሳየት ተዘጋጅተናል።

0
88
ከ5 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ጨዋታን ለማስተናገድ የተዘጋጀችው ባሕር ዳር ከተማ ሞቅ ሞቅ ብላለች። ዛሬ ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር ለሚደረገው ወሳኝ ፍልሚያ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ከማለዳው ጀምሮ በስታዲየሙ መግቢያ በሮች ላይ ተሰልፈው ይገኛሉ።
የብሔራዊ ቡድኑ መለያዎችን እና የሀገር ሰንደቅ ዓላማ ያሸበረቁት የከተማዋ ነዋሪዎች፣ በሜዳው ተገኝተው እስከ መጨረሻው እንደ “12ኛ ተጫዋች” ቡድናቸውን ለማበረታታት ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል።
የባሕር ዳር አለማቀፍ ስታዲየም ከዚህ ቀደም አይቮሪኮስትን 2 ለ 1 ያሸነፈበትን ታሪካዊ ጨዋታ ጨምሮ ከተደረጉ 8 የነጥብ ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ የተሸነፈበት የዋልያዎቹ የድል ምድር ሲኾን፣ ደጋፊዎቹም ዛሬ በድጋፋቸው ሴኔጋልን ለማሸነፍ የራሳቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here