በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ምድብ አንድ በተደረጉ ጨዋታዎች ፈረንሳይ ቤልጂየምን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ስታሸንፍ፣ ጣሊያን በበኩሏ ቱርክን 4 ለ 1 ረታለች።
በምድብ ሁለት በተካሄዱ መርሐ ግብሮች ደግሞ ሞንቴኔግሮ አርሜንያን 3 ለ 2 በኾነ ውጤት ያሸነፈች ሲኾን፣ በጆርጂያ እና ዩክሬን፣ በላቲቪያ እና ሳይፕረስ እንዲሁም በሰሜን አየርላንድ እና ሀንጋሪ መካከል የተደረጉት ሦሥቱም ጨዋታዎች ያለ ምንም ግብ በዜሮ ለዜሮ አቻ ውጤት ተጠናቀዋል።
በምድብ አራት በኩል ቦስኒያ ሄርዞጎቪና ሮማኒያን 4 ለ 2 ስታሸንፍ፣ ስዊድን በበኩሏ ፖላንድን 3 ለ 1 በማሸነፍ ድል ቀንቷታል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_19_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



