የአርሰናል ጉዞ አስካሁን የሚያቆም አልተገኘም ዛሬ ብራይተን ይሳካለት ይኾን?

0
117

 

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ5ኛ ሳምንት መርሐ ግብሮች ዛሬ የሚቀጥሉ ሲኾን አመሻሽ 11፡00 ላይ ሻምፒዮኑ አርሰናል ወደ አሜክስ ስታዲየም አቅንቶ ብራይተንን ይገጥማል።

አርሰናል እስካሁን በሁሉም ውድድሮች በስምንት ጨዋታዎች ማሸነፍ ችሏል። በሊጉም አራቱንም ሳምንታት በድል በማጠናቀቅ በ12 ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡን እየመራ ይገኛል።

ቡድኑ በአራቱ ሳምንታት አንድ ግብ ብቻ በማስተናገድ ጠንካራ የመከላከል አቅም ያሳየ ሲኾን፣ በግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ ድንቅ ብቃት ላይ ትልቅ ዕምነት ጥሏል። ዛሬ ግን ዴቪድ ራያ የሚፈተንበት ነው።

በሰባት ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ብራይተን በበኩሉ፣ በአራቱ ጨዋታዎች 13 ግቦችን በማስቆጠር የሊጉን መሪዎች ጭምር የሚበልጥ የአጥቂ ኀይል እንዳለው አሳይቷል። ኾኖም በዛሬው ጨዋታ ስቲፋኖስ ዚማስ እና ያንኩባ ሚንቴህ በጉዳት አይሰለፉም።

በሌሎች የዛሬ የሊጉ መርሐ ግብሮች፡-

👉ቀን 8፡30 ቶተንሀም ከ አስቶንቪላ

👉ቀን11፡00 ኤቨርተን ከ ኢፕስዊች

👉ቀን11፡00 ኒውካስል ከ ሃል ሲቲ

👉ምሽት1፡30 ኖቲንግሃም ፎረስት ከኮቨንትሪ ሲቲ

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_09_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here