የሦሥት ሳምንት የእረፍት ጊዜ በአሠልጣኞች ላይ ጫናን ደቅኗል።
የሦሥት ሳምንታት የብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታዎች እረፍት ከመጀመሩ በፊት ውጤት የራቃቸው የክለብ አሠልጣኞች በከፍተኛ ጫና እና የሥራ ስንብት ስጋት ውስጥ ወድቀዋል።
የፉልሃሙ አለቃ
አልቫሮ አርቤሎአ በክረምቱ ኀላፊነት ከተረከቡ በኋላ በመጀመሪያዎቹ 4 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ምንም ድል አላስመዘገቡም በተጨማሪም በተጫዋቾች ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተፈጠረ ያለው ጫና ምክንያት በቡድኑ ውስጥ አለመረጋጋት እንዳለ ይነገራል።
ሌላው የማንቸስተር ዩናይትድ አለቃ ማይክል ካሪክ ናቸው በሊግ ካፕ በብራይተን 3 ለ 2 ተሸንፈው መውጣታቸው
እና በ10 ተጫዋቾች ብቻ በተጫዎተው ማንቸስተር ሲቲ መረታታቸው በካሪክ ላይ ያለውን ጫና አክብዶታል።
ዛሬ ምሽት 12፡30 በክራቨን ኮቴጅ በፉልሃም እና ማንቸስተር ዩናይትድ መካከል የሚደረገው ጨዋታ ለሁለቱም አሠልጣኞች ከእረፍቱ በፊት እፎይታን የሚያገኙበት ወሳኝ ፍልሚያ ይኾናል ብሏል ቢቢሲ በዘገባው።
በማንቸስተር ዩናይትድ በኩል ማቲያስ ዴ ሊክት፣ አማድ ዲያሎ እና ማኑኤል ኡጋርቴ በጉዳት የማይሰለፉ ሲኾን ሉክ ሾው ከጉዳት አገግሞ ተመልሷል። አዲሱ ፈራሚ ካርሎስ ባሌባም የመሰለፍ ዕድል ሊያገኝ ይችላል። በፉልሃም በኩል ራያን ሴሴኞን ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሥብሥቡ ተመልሷል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_10_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



