በ4ኛው ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ መርሐግብር ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ ተጫዋቾች ይፋ ተደርገዋል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ4ኛ ሳምንት የቅዳሜ ጨዋታዎች ከፍተኛ ነጥብ የተመዘገበባቸው ኾነው አልፈዋል።
ምርጥ ከተባሉት መካከል የፊት መሥመሩን ተቆጣጥሯል ኬቪን ሻዴ። ብሬንትፎርድ ከቦርንመዝ 2 ለ 2 በተለያየበት ጨዋታ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር እና ሦሥት የቦነስ ነጥቦችን በመውሰድ የሳምንቱን ከፍተኛ ነጥብ ሠብሥቧል።
ሌላው እና ሁለተኛ ላይ የተቀመጠው ዳቪድ ራያ ሲኾን አርሰናል ሰንደርላንድን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ ግብ ሳይቆጠርበት ከመውጣቱም በላይ የኤንዞ ሌ ፌን የፍጹም ቅጣት ምት በማዳን 14 ነጥብ አስመዝግቧል።
በተመሳሳይ ነጥብ ከምርጥ ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ የሰፈረው ሌፍ ዴቪስ ነው። አንድ ግብ በማስቆጠር እና ሁለት አመቻችቶ በማቀበል ከራያ ጋር እኩል 14 ነጥብ ማግኘት ችሏል።
ሞሃመድ ቤሉሚ ደግሞ 13 ነጥብ በማግኘት ምርጥ ተጫዋች ተብሏል። ኸል ሲቲ ከቼልሲ ጋር 2 ለ 2 ባደረገው ጨዋታ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ከከፍተኛ ነጥብ ሠብሣቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተካትቷል።
ለእናንተስ የትኞቹ
ተጫዋቾች ምርጥ ነበሩ?
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



