የማንቸስተር ሲቲው አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ በፕሪሚየር ሊጉ የማንቸስተር ደርቢ ታሪክ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመኾን አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።
ኖርዌያዊው አጥቂ ማንቸስተር ሲቲ በኦልድ ትራፎርድ ማንቸስተር ዩናይትድን 1 ለ 0 በረታበት 199ኛው የማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ በ60ኛው ደቂቃ ላይ የቡድኑን የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል።
በዚህም ግብ ሀላንድ በፕሪሚየር ሊጉ ማንቸስተር ዩናይትድ ላይ ያስቆጠራቸውን የግብ ብዛት ወደ 9 አድርሷል።
በፕሪሚየር ሊጉ የማንቸስተር ደርቢ ታሪክ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትን ከዚህ በፊት ሰርጂኦ አጉኤሮ
እና ዌይን ሩኒ በ8 ግቦች ተጋርተው ቆይተዋል።
ሀላንድ አሁን የተገኘውን ድንቅ ሪኮርድ ለማስመዝገብ የፈጀበት 8 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ብቻ መኾኑን ስካይ ስፖርት አስነብቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



