ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በ5ሺ ሴቶች የዓለም አትሌቲክስ አልቲሜት ሻምፒዮን ሺፕ ይጠበቃሉ።

0
102
ለ3 ተከታታይ ቀናት በሀንጋሪ ቡዳፔስት ሲካሄድ የቆየው የዓለም አትሌቲክስ አልቲሜት ሻምፒዮን ሺፕ ውድድር ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል።
ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ ባለው በዚሁ ውድድር የመጨረሻ ቀን በሴቶች 5ሺ ሜትር 6 ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ይሳተፋሉ።
ከእነዚህም መካከል በርቀቱ ልቅና አምባው 14:18:41፣ አለሺኝ ባወቀ 14:18:54፣ ፍሬወይኒ ኃይሉ 14:18:94 የግል ምርጥ ሰዓት አላቸው።
አትሌቶቹ የግል ምርጥ ሰዓታቸውን ያስመዘገቡት በዚህ ዓመት በተካሄደው የሮም ዳይመንድ ሊግ ሲኾን ከእነዚህም መካከል ፍሬወይኒ ኃይሉ ትናንት በ1ሺ 500 ሜትርም ተሳትፋ 4ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች።
በዛሬው 5ሺ ሜትር የሚወዳደሩት ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ሂሩት መሸሻ፣ ሰናይት ጌታቸው እና ፋንታዬ በላይነህ መኾናቸውን የውድድሩ አዘጋጆች ይፋ ያደረጉት የተሰላፊዎች ዝርዝር ያመለክታል።
ይሄው የሴቶች 5ሺ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ዛሬ ምሽት 2:10 ላይ ይጀመራል።
በኃይሌ አበራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here