‎ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ በማንችስተር ዩናይትድ ዛሬ የመጀመሪያ ሥራቸውን ይጀምራሉ።

0
62

ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝነታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ዛሬ ኅዳር 9/2019 ዓ.ም የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሠልጣኝ ኾነው ሥራቸውን በይፋ ይጀምራሉ።

አሠልጣኝ ማይክል ካሪክን በመተካት ባለፈው ሳምንት የተሾሙት አርጀንቲናዊው አሠልጣኝ እስከ 2029 የሚዘልቅ ውል ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ መሠረት በኮንካፍ ኔሽንስ ሊግ ሩብ ፍጻሜ ከሃይቲ ጋር የተደረጉትን ሁለት ጨዋታዎች መርተው እንዲያጠናቅቁ ተፈቅዶላቸው ነበር።

ፖቸቲኖ ከአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን መለያየት በሕይወታቸው “በጣም ከባድ” ውሳኔ መኾኑን ገልጸው፣ ሹመታቸው ይፋ ከተደረገ በኋላ በተካሄደው የመጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሲያለቅሱ ተስተውለዋል።

አሠልጣኙ ሃይቲን 6 ለ 0 እና በሲንሲናቲ በተደረገው የመጨረሻ ጨዋታቸውም 2 ለ 0 በማሸነፍ በድምር ውጤት 8 ለ 0 አጠናቅቀው በቀጥታ ወደ እንግሊዝ በረራ አድርገዋል።

የ54 ዓመቱ አሠልጣኝ ዛሬ በእንግሊዝ ሰዓት አቆጣጠር ቀትር አካባቢ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_09_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here