በአውሮፓ የውድድር መድረክ ስኬታማ ከኾኑ ክለቦች አንዱ ማንቸስተር ዩናይትድ ለተከታታይ ሦሥት ዓመታት ከቻምፒዮንስ ሊጉ ርቆ ቆይቷል፡፡
ዘንድሮ ግን ወደ ውድድሩ ተመልሶ ዛሬ ምሽት የመጀመሪያ ጨዋታውን ከአዘርባጃኑ ሳባህ ክለብ ጋር በሜዳው ያደርጋል፡፡
ከጨዋታው አስቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትዱ አሠልጣኝ ማይክል ካሪክ በሰጠው አስተያየት ቻምፒዮንስ ሊጉ ምን ያክል ልዩ እና አስፈላጊ መድረክ እንደኾነ የምታውቀው ርቀህ ስትቆይ ነው፤ስትመለስ ግን እንደገና ላለመራቅ የምትችለውን ሁሉ ታደርጋለህ ብሏል፡፡
አሠልጣኙ አያይዞም ለተጋጣሚያቸው ዝቅተኛ ግምት ሳይሰጡ እንደሚገቡ እና የቻምፒዮንስ ሊግ ውድድራቸውን በጥሩ ውጤት ለመጀመር እንደተዘጋጁ ተናግሯል፡፡
በጨዋታው አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ያክል በጉዳት ከሜዳ ርቆ የቆየው ኔዘርላንዳዊው ተከላካይ ማቲያስ ዲሊት ከጉዳቱ አገግሞ ሊሰለፍ እንደሚችል ተነግሯል፡፡
ማንቸስተር ዩናይትድ በአውሮፓ የውድድር መድረክ ከአዘርባጃን ክለብ ጋር ሲጫወት የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ መኾኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ቀያይ ሰይጣኖቹ ለመጨረሻ ጊዜ በቻምፒዮንስ ሊጉ ውድድር የተሳተፉት በ2023/24 የውድድር ዓመት ሲኾን በወቅቱ ከምድብ መርሐግብር ነበር የተሰናበቱት፡፡
የዛሬው የማንቸስተር ዩናይትድ እና ሳባህ ጨዋታ ምሽት 4፡00 ላይ በዩናይትድ ሜዳ ኦልድትራፎርድ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡
በኃይሌ አበራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



