አዲስ የውድድር መድረክ የሆነው የወርልድ አትሌቲክስ አልቲሜት ቻምፒዮንሺፕ የመጀመሪያ ቀን ምሽቱን ትናንት በሀንጋሪ ቡዳፔስት አከናውኗል።
በመክፈቻው ዕለት ከተደረጉ ውድድሮች ውስጥ አንዱ የሆነው የወንዶች 5ሺህ ሜትር ውድድር ብርቱ ፉክክር ታይቶበታል።
ኖርዌያዊው ጃኮብ ኢንግብሪስተን በጥሩ ብቃት ቀዳሚ ኾኖ ጨርሷል። ተከታዩን ደረጃ ለማግኘት እልህ አስጨራሽ ፉክክር ሲታይ ኢትዮጵያን የወከለው ቢንያም መሃሪ 4ኛ ኾኖ ገብቷል። ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አዲሱ ይሁኔ ውድድሩን ሳይጨርስ ቀርቷል።
አሜሪካዊያን አትሌቶች ሌሎችን እስከ 7 ያሉ ደረጃዎችን አግኝተዋል።
በ800 ሜትር ሴቶች በተደረገ የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያን የወከለችው ንግሥት ጌታቸው 3ኛ ኾና በማጠናቀቅ ዛሬ ምሽት ለሚካሄደው የፍፃሜ ውድድር ደርሳለች።
ትናንት በአጠቃላይ 8 የፍፃሜ ውድድሮች ተደርገዋል። አንደኛ በመውጣት ያሸነፉ አትሌቶችም 110 የአሜሪካን ዶላር እና ዋንጫ ተሸልመዋል። ዛሬ ምሽት ሌሎች የፍፃሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
ባሕር ዳር #መስከረም_02/2019_ዓ_ም
በሰኢድ ኢብራሂም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



