ሞሮኮ የ2030 የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታን የማስተናገድ ፍላጎት ይሳካ ይኾን?

0
87
ከአራት ዓመት በኋላ የሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ውድድር በተለየ ሁኔታ በሦሥት አህጉራት እና በስድስት ሀገራት አስተናጋጅነት ይከናወናል፡፡
በ2030 100ኛ ዓመቱን የሚደፍነውን የዓለም ዋንጫ ኡራጓይ፣ አርጀንቲና እና ፓራጓይ የመጀመሪያ ሦሥት የመክፈቻ ጨዋታዎችን በማስተናገድ ውድድሩን ያስውባሉ፡፡
ሞሮኮ፣ ስፔን እና ፖርቹጋል ደግሞ በጥምረት ቀሪ ጨዋታዎችን ያስተናግዳሉ፡፡ ከውድድሩ መድረስ አስቀድሞ ግን ስፔን እና ሞሮኮ የፍጻሜው ጨዋታ በሀገራቸው እንዲደረግ ከወዲሁ እየተፎካከሩ ይገኛሉ፡፡
የስፔን እግር ኳስ ማኅበር በሳንቲያጎ ቤርናባው እንዲደረግ ይፈልጋል፡፡ ዛሬ ደግሞ የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፎዚ ሌክጃ ፍጻሜውን ካዛብላንካ ላይ ለማድረግ በጽኑ ፍላጎት እየሠሩ ስለመኾናቸው ያሁ ስፖርትስ ዘግቧል፡፡
ሞሮኮ የፍጻሜውን ጨዋታ ለማግኜት በዓለም ቀዳሚ የኾነ 115 ሺህ ተመልካች የሚይዝ ስታዲየም በካዛብላንካ አቅራቢያ መገንባት ጀምራለች፡፡
ስፔን እና ሞሮኮ የፍጻሜውን ጨዋታ ለማስተናገድ በየፊናቸው ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረጉ ቢኾንም የውድድሩ ባለቤት ፊፋ ግን እስካሁን ይፋዊ ውሳኔ አልሰጠም፡፡
በንዋይ ሙሉጌታ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here