አንቶኒዮ ሩዲገር ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ራሱን አገለለ፡፡

0
116
የ33 ዓመቱ የሪያል ማድሪድ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች አንቶኒዮ ሩዲገር የሀገሩን መለያ ለብሶ እንደማይጫወት አስታውቋል፡፡
በጀርመን ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ልምድ ካላቸው እና በብሔራዊ ቡድኑ ለረዥም ዓመት ከቆዩት ተጫዋቾች መካከል የኾነው ሩዲገር ለወጣቱ ትውልድ ዕድል ለመስጠት በሚል ከብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡
አንቶኒዮ ሩዲገር የጀርመን ብሔራዊ ቡድን መለያ ለብሶ ከታዳጊ ቡድኑ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ ተጫውቶ አሳልፏል፡፡
በዋናው ቡድን እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን ከ2014 ጀምሮ 86 ጨዋታዎችን አድርጎ ሦሥት ግብ አስቆጥሯል፡፡
ሩዲገር በሩሲያ አዘጋጅነት በተካሄደው የኮንፌደሬሽን ዋንጫን ላይ ጀርመን ቺሊን አሸንፋ ዋንጫ ስታነሳ የብሔራዊ ቡድኑ አካል ነበር፡፡
በዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here