አዲስ ክብረወሰን የተመዘገበበት ዝውውር።

0
160
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር ጊዜ ሌሊቱን ተጠናቅቋል።
በዚህ የዝውውር ወቅት ክለቦች 3 ነጥብ 48 ቢሊዮን ፓውንድ በማውጣት ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት ታሪካዊ የገንዘብ ወጭ ክብረወሰንን ሰብረዋል።
ይህ አዲስ ክብረወሰን የተፃፈው ባለፈው የዝውውር ጊዜ የተመዘገበውን የ3 ነጥብ 14 ቢሊዮን ፖወንድ ከፍተኛ ወጭ በመሻገር ነው።
ማንቸስተር ሲቲ የአርጀንቲናዊውን አማካኝ ኤንዞ ፈርናንዴዝን ከቼልሲ በጋራ የእንግሊዝ ዝውውር ክብረወሰን በኾነው 125 ሚሊዮን ፖወንድ ወጭ በማስፈረም የራሱን የዝውውር ታሪክ በዚሁ ክረምት አሻሽሎታል።
ሊቨርፑል ፈረንሳዊውን አጥቂ ብራድሌይ ባርኮላን ከፒኤስጂ በ123 ሚሊዮን ፓወንድ ሲያስፈርም ቼልሲ ደግሞ ሞርጋን ሮጀርስን በ117 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ሥብሥቡ ቀላቅሏል።
ማንቸስተር ሲቲም ኤሊዮት አንደርሰንን በ116 ሚሊዮን ፓውንድ አስፈርሟል።
በዚህ የዝውውር ጊዜ ማንቸስተር ሲቲ ከፍተኛውን ወጭ አፍስሷል። 440 ነጥብ 3 ሚሊዮን ፓወንድ ሲያወጣ፣ ቼልሲ በ347 ሚሊዮን ፓውንድ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ቼልሲ ከተጫዋቾች ሽያጭ ከ357 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ በማግኘት ሌላ ክብረወሰን ማስመዝገቡን ቢቢሲ እና ስካይ ስፖርትስ ዘግበዋል።
በሰኢድ ኢብራሂም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here