ስፖርትን በታሪክ።

0
124
ሌኖክስ ሉዊስ የቀድሞ ታዋቂ እንግሊዛዊ-ካናዳዊ ፕሮፌሽናል ቦክሰኛ ሲኾን በዓለም ቦክስ ታሪክ ውስጥ ከምንጊዜውም ምርጥ የከባድ ሚዛን ሻምፒዮኖች አንዱ ነው። እ.ኤ.አ ከ1989 እስከ 2003 በነበሩት ዓመታት ውስጥ ሦሥት ጊዜ የዓለም ከባድ ሚዛን ሻምፒዮን መኾን የቻለው ሌኖክስ ሉዊስ ማንም ያልተከፋፈለው ፍጹም የዓለም ሻምፒዮን መኾንም ችሏል።
ረጅም ቁመቱ (6 ጫማ ከ5 ኢንች) እና ጠንካራ ጡጫው ከከፍተኛ የቦክስ ስልት እና ብልሃት ጋር ተደምሮ “አንበሳው” (ዘላየን) የሚል ቅጽል ስም አስገኝቶለታል።
በ1988 በሴኡል ኦሊምፒክ ካናዳን በመወከል በከባድ ሚዛን ዘርፍ የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፏል። በሕዳር 1999 ኢቫንደር ሆሊፊልድን በማሸነፍ የዓለም ከባድ ሚዛን ሻምፒዮንም ኾኗል። ይህንን ክብር ለ25 ዓመታት ያህል ለብቻው ይዞ የቆየ የመጨረሻው ቦክሰኛም ነበር።
በቦክስ ሕይወቱ 41 ግጥሚያዎችን አሸንፏል። 2 ተሸንፎ፣ 1 ደግሞ አቻ ወጥቷል። በታሪኩ የደረሱበትን ሁለቱን ሽንፈቶች (በኦሊቨር ማክኮል እና በሀሲም ራህማን) የደረሱበትን ሽንፈቶች በድጋሚ ጨዋታ በዝረራ በማሸነፍ ኃያልነቱን አሳይቷል።
በ2004 ዓ.ም ከቦክስ ዓለም ሲሰናበት በነገሰበት የሻምፒዮንነት ክብር ላይ ነበር። የመጨረሻዎቹ ሁለት ጨዋታዎቹ ማይክ ታይሰንን በ2002 እና ቪታሊ ክሊችኮን በ2003 ያሸነፈባቸው ታሪካዊ ጨዋታዎችም ነበሩ።
በፕሮፌሽናል ቦክስ መዝገብ ከአጠቃላይ ጨዋታዎች 44 በማሸነፍ (32ቱን በዝረራ)፣ 2 ሽንፈት እና 1 አቻ (ከኢቫንደር ሆሊፊልድ ጋር) አስመዝግቧል።
ሌኖክስ ሉዊስ ከቦክስ ስፖርት ከተሰናበተ በኋላ ወደ ሚዲያ እና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ተሻግሯል። ለታዋቂዎቹ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች (እንደ ኤችቢኦ እና ፎክስ ስፖርት ያሉ) የቦክስ ጨዋታዎችን በከፍተኛ ሙያዊ ብቃት በመተንተን እና አስተያየት በመስጠት ለዓመታት ሰርቷል።
ከዚህ በተጨማሪ ሊኖክስ ሊዊስ ሊግ ኦፍ ቻምፒዎን ፋውንዴሽን የተባለ የራሱን ፋውንዴሽን በማቋቋም ታዳጊ ወጣቶችን በስፖርት እና በትምህርት የማብቃት ሥራ ይሠራል፤ በአሁኑ ወቅት ሕይወቱን በሚያሚ፣ ቶሮንቶ እና ጃማይካ እያፈራረቀ ይመራል።
ይህ ድንቅ ቦክሰኛ ዛሬ የተወለደበትን 61ኛ ዓመት የልደት በዓሉን እያከበረ መኾኑን ዚስ ዴደይ ኢን ስፖርት ሀመስትሪ የተሰኘ ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡
በአማኑኤል ፀጋዬ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here