ኢንስትራክተር መብራቱ ሀብቱ ፋሲል ከነማን ተቀላቀለ።

0
31
በአሰልጣኝ ዘማሪያም ወልደ ጊዮርጊስ የሚመሩት አፄዎቹ አዲስ ምክትል አሰልጣኝ ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል።
ኢንስትራክተር መብራቱ ሀብቱን በሁለት አመት ውል አስፈርመዋል።
ኢንስትራክተር መብራቱ ሀብቱ በባህርዳር ከተማ ምክትል አሰልጣኝ እና የቪድዮ ትንተና ባለሙያ እንዲሁም ቴክኒካል ዳይሬክተርነት አገልግለዋል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በቪዲዮ ተንታኝነት ከመስራታቸው ባለፈ የተለያዩ ልምዶችንም ከሀገር ውጭ ጭምር አካብተዋል።
ኢንስትራክተር መብራቱ ሀብቱ ታዲያ አሁን በሁለት አመት ውል የፋሲል ከነማ ምክትል አሰልጣኝ ሆነው ለማገልገል መሾማቸውን የክለቡ ይፋዊ ገፅ አስነብቧል።
መለሰ ግዛቸው
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here