በኬንያ ላለፋት ቀናት ሲደረግ የቆየው የአፍሪካ ዞን 5 ወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ትናንት ምሽት ተጠናቋል።
ቀጠናዊ ትስስርን ማጠናከርና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ለአለም ወጣቶች ኦሎምፒክ የተሻለ ተፎካካሪ እንዲሆኑ መንገድ መክፈት የውድድሩ አላማ ነበር።
በውድድሩ 10 ሀገራት በ7 የስፓርት አይነቶች ተፎካክረዋል። በ4 የስፓርት አይነት ብቻ የተሳተፈችው ኢትዮጵያ 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
ከተሳተፉበት 4 ውድድር በ3ቱ ሜዳልያ ያስመዘገቡት የኢትዮጵያ ልኡክ አባላት በጥቅሉ 12 ሜዳልያዎችን ሰብስበዋል።
ከ3 በ 3 የሴቶች ቅርጫት ኳስ ውድድር በስተቀር በሌሎች ሜዳልያ ተመዝግቧል።
የኢትዮጵያ ልኡክ 6 ወርቅ 4 ብር እና 2 ነሀስ በ12 ሜዳልያ 3ኛ ሆኖ ጨርሷል።
አስተናጋጇ ኬንያ በ22 ወርቅ እና በአጠቃላይ 51 ሜዳልያ እንዲሁም ኡጋንዳ ከኢትዮጵያ እኩል 6 ወርቅ አስመዝግባ በብር እና ነሀስ በልጣ 2ኛ ሆናለች።
የኢትዮጵያ ልኡክ ዛሬ የሚመለስ ይሆናል። አቀባበልም ይደረግለታል።
መለሰ ግዛቸው
#ባሕር_ዳር፡ ፤ 22/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



