በአፍሪካ ዞን 5 ሀገራት ወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዛሬም በድል ጎዳና ቀጥለዋል።

0
38
ዛሬ 3 ሜዳልያዎች ሲመዘገቡ በሁለት ቀን የኢትዮጵያ ልኡክ ሜዳልያ 11 ደርሷል።
ዛሬም በአትሌቲክስ እና ብስክሌት የወርቅ ሜዳልያዎች ተመዝግበዋል።
በአትሌቲክስ ሴቶች 1500 ሜትር ሩጫ ኤልሳቤት አማረ አሸንፋለች።
በብስክሌት ወንዶች ለገሰ ሰለሞን ወርቅ ሜዳልያ ሲያስመዘግብ በውድድሩ 2ኛ ወርቁ ሆኗል።
በሴቶች የብስክሌት ውድድር ደግሞ ማህደር ደስታ ነሀስ አስገኝታለች። ትናንት ብር ሜዳልያ ማስመዝገቧ ይታወሳል።
ኢትዮጵያ እስካሁን ሰአት 6 ወርቅ ፣ 3 ብር እና 2 ነሀስ 11 ሜዳልያ አስመዝግባለች።
መለሰ ግዛቸው
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here