የአፍሪካ ዞን 5 ወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ትናንት በኬንያ ተጀምሯል።
ቀጠናዊ ትስስርን ማጠናከርና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ለአለም ወጣቶች ኦሎምፒክ የተሻለ ተፎካካሪ እንዲሆኑ መንገድ መክፈት የውድድሩ አላማ ነው።
ዛሬ በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ እና ብስክሌት አሸንፋለች።
በአትሌቲክስ 3 ወርቅና 1 ብር ተመዝግቧል። የወርቅ ሜዳልያ ያስመዘገቡት በሴቶች ሲሆን ዮርዳኖስ ፀጋአብ በ3ሺ ሜትር ፣ ነፃነት ሰለሞን በ800 ሜትር እና ኒያሚን ኑረዲን በ5 ኪ.ሜ ርምጃ ውድድር ነው።
የብር ሜዳልያ ያስገኘው ደግሞ በወንዶች 1500 ሜትር ዋሚ ዋጅራ ነው።
በብስክሌት በተደረጉ የሰአት ሙከራ ውድድሮች ሜዳልያዎች ተመዝገበዋል።
በወንዶች ለገሰ ሰለሞን ወርቅ ሲያስገኝ ማህደር ደስታ በሴቶች ብር አስመዝግባለች።
እስካሁን ኢትዮጵያ በዛሬ ውሎ ብቻ 4 ወርቅና 2 ብር ባለቤት ሆናለች።
መለሰ ግዛቸው
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



