ኢትዮጵያ ተሳታፊ የሆነችበት የአፍሪካ ሀገራት ኦሎምፒክ ኮሚቴ የዞን 5 ውድድር ትናንት በኬንያ ተጀምሯል።

0
28
ቀጠናዊ ትስስርን ማጠናከርና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ለአለም ወጣቶች ኦሎምፒክ የተሻለ ተፎካካሪ እንዲሆኑ መንገድ መክፈት የውድድሩ አላማ ነው።
ለ አምስት ቀናት በሚቆየው ውድድር ኢትዮጵያን ጨምሮ 11 ሀገራት ተሳታፊ ናቸው።
በኬንያ ናይሮቢ ኬንያታ ዩንቨርስቲ የሚደረገው ውድድር በ ሰባት የስፓርት አይነቶች በሁለቱም ፃታ ይከወናል።
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በ 4 ስፓርት አይነቶች ተሳታፊዎችን የዞ ወደ ስፍራው አቅንቷል።
በአትሌቲክስ ፣ ውሀ ዋና እና ብስክሌት በሁለቱም ፃታ እንዲሁም በ3ለ3 ሴቶች ቅርጫት ኳስ ኢትዮጵያ ተሳታፊ ናት ።
ውድድሩ ትናንት የተጀመረ ሲሆን ቅዳሜ ይጠናቀቃል።
መጃውን ከአኖካ ገፅ አግኝተናል ።
መለሰ ግዛቸው
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here