ስፖርትን በታሪክ

0
50
ከ2001 እስከ 2006 እ.ኤ.አ ባሉት ዓመታት የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን “ወርቃማ ትውልድ”ን በመምራት የመጀመሪያው የውጭ አገር ዜጋ ናቸው።
በተለያዩ ሃገራት 18 ዋና ዋና ዋንጫዎችን በማሸነፍ ለ35 ዓመታት የተሳካ የአሰልጣኝነት ሕይወት አሳልፈዋል።
በሃገራቸው ክለብ ጎተንበርግ እ.ኤ.አ በ1982 የዩኤፋ ካፕ፣ በቤንፊካ ሦስት የፖርቱጋል ሊግ ዋንጫዎችን አሸንፈዋል። በላዚዮም የጣሊያን ሴሪኤ ዋንጫን፣ የዩኤፋ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን እና የዩኤፋ ሱፐር ካፕን አሳክተዋል።
ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር በሦስት ዋና ዋና ውድድሮች (የ2002 ዓለም ዋንጫ፣ ዩሮ 2004 እና የ2006 ዓለም ዋንጫ) ቡድኑን እስከ ሩብ ፍጻሜ ማድረስ ችለዋል።
በተጨማሪ በአሠልጣኝነት ዘመናቸው ማንቸስተር ሲቲን፣ ሌስተር ሲቲን፣ የሜክሲኮ እና የኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድኖችንም አሰልጥነዋል።
በ2024 መጀመሪያ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የደረሰ የካንሰር ህመም እንዳለባቸው ለሕዝብ ይፋ ካደረጉ በኋላ በስማቸው በተሰራው ዘጋቢ ፊልም ላይ “አትዘኑ፣ ፈገግ በሉ” በማለት ልብ የሚነካ የመጨረሻ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ታዋቂው የስዊድን እግር ኳስ ተጫዋች እና አሰልጣኝ ስቬን-ጎራን ኤሪክሰን በዛሬዋ ዕለት እ.ኤ.አ ነሐሴ 26 ቀን 2024 ነበር በ76 ዓመታቸው በጣፊያ ካንሰር ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።
አማኑኤል ፀጋዬ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here