ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እየተሠራ ነው።

0
36

 

በፍኖተሰላም ከተማ በስድስት ክለቦች መካከል ሲካሄድ የቆየው የእርስ በእርስ የክረምት የእግር ኳስ ጨዋታ ውድድር ተጠናቅቋል።

የፍኖተሰላም ከተማ አሥተዳደር ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ቢኒያም ጌጡ ወጣቶች እና ታዳጊዎች በትርፍ ጊዜያቸው በስፖርት ላይ እንዲያሳልፉ በማድረግ በአዕምሮ እና አካል የዳበረ ትውልድ ለመገንባት እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተለይ ሥልጠናዎችን እና ውድድሮችን አጠናክሮ በማስቀጠል ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እየተሠራ መኾኑን አስረድተዋል። ስፖርቱ ሕዝባዊ እንዲኾን ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት ለመሥራት ትኩረት መሰጠቱንም ጠቁመዋል።

የፍኖተሰላም ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዮናስ ሞላ ስፖርታዊ ውድድሩ በወጣቶች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር እና መነሳሳትን የሚፈጥ ነው ብለዋል።

በተለይ ውድድሩ ስፖርቱ ሕዝባዊ መሠረት እንዲኖረው ከፍተኛ ሚና እየተወጣ እንደኾነም ጠቁመዋል።

በምዕራብ ጎጃም ዞን ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ የስፖርት ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉየለት ገበየሁ ወጣቶች እና ታዳጊዎች የክረምት ወቅትን በስፖርት እንዲያሳልፉ በሁሉም ወረዳዎች ውድድሮች እና ሥልጠናዎች እየተካሄዱ መኾናቸውን አንስተዋል።

በዞኑ ከ30 ሺህ በላይ ወጣቶች እና ታዳጊዎች በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች በውድድር እና ሥልጠና እየተሳተፉ ናቸው ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት የተቀዛቀዘውን ስፖርት በማነቃቃት ተወዳዳሪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ጠቁመዋል።

አስተያየታቸውን ለአሚኮ የሰጡ ተጫዋቾች እየተካሄዱ ያሉ ስፖርታዊ ውድድሮች ያላቸውን ተሳትፎ እና መነቃቃት እየጨመረ መኾኑን ተናግረዋል።

ቀጣይ ልምምዶችን እና ሥልጠናዎችን በመውሰድ በሌሎች ውድድሮች ላይ የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ እንደሚተጉ ነው ያስረዱት።

በውድድሩ ማጠቃለያ ላይ ካሳ ሞገስ የእግር ኳስ ክለብ ከፍኖተሰላም 01 ቀበሌ ክለብ ተገናኝተው ካሳ ሞገስ ክለብ በማሽነፍ የዋንጫ ባለቤት ኾኗል።

#አሚኮ #ስፖርት #ኢትዮጵያ 🇪🇹

#ፍኖተ_ሰላም #ነሐሴ_19_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ ፦ ንጉሥ ስንታየሁ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here