ቶተንሀም ሳቪኒዮን በ75 ሚሊዮን ፖውንድ ከማንቸስተር ሲቲ አስፈረመ።

0
39
ቶተንሀም ሆትስፐር ብራዚላዊውን የክንፍ መስመር ተጫዋች ሳቪኒዮን ከማንቸስተር ሲቲ በቋሚ ዝውውር ማስፈረሙን በይፋ አረጋግጧል።
ቶተንሀም ለተጫዋቹ ዝውውር አሁን 75 ሚሊዮን የሚከፍል ሲሆን፣ ከተጫዋቹ ብቃት ጋር ተያይዞ በሚከፈሉ ማበረታቻዎች አጠቃላይ ዋጋው እስከ 85 ሚሊዮን ፖውንድ ሊደርስ ይችላል።
ይህ ዝውውር ማንቸስተር ሲቲ በተጫዋች ሽያጭ ካገኘው ከፍተኛው የገንዘብ መጠን በመሆን አዲስ የክለቡን ክብረወሰን ሰብሯል።
በአሰልጣኝ ሮቤርቶ ዴ ዘርቢ የሚመራው ቶተንሀም በዚህ የዝውውር መስኮት ያወጣው አጠቃላይ ወጪ ከ300 ሚሊዮን ፖውንድ በላይ ደርሷል።
ዳናይት ሲሳይ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here