የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች የሴካፋ ዞን ሻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ 2ኛ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ።

0
57
በሩዋንዳ ኪጋሊ በ10 ቡድኖች መካከል በሚደረገው ፋክክር ንግድ ባንክ በምድብ ሁለት ይገኛል።
ሶስት ክለቦች በሚገኙበት ምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን የጅቡቲውን ኡጅኮ 11ለ0 አሸንፏል። ድሉም በዞኑ ውድድር ታሪክ ክብር ወሰን ነው።
ዛሬ ከምድቡ ለማለፍ እና የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚ መሆኑን ለማረጋገጥ ከኡጋንዳው ክዋምፔ ሙስሊም ሌዲስ ጋር ይጫወታል።
ጨዋታውን ካሸነፈ ከምድቡ አንድ ክለብ ብቻ በሚሻገርበት ጠባብ እድል ማለፋን ያረጋግጣል።
ጨዋታው 11:00 ሲል ይደረጋል።
መለሰ ግዛቸው
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here