በሲሌሲያ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ ሆኑ።

0
55
በ13 ተኛ የውድድር ከተማ በሆነችው ፖላንድ ሲሌሲያ ገመቹ ጎዳና እና ፅጌ ድጉማ ባለ ድል ሆነው አጠናቀዋል።
በፖላንድ ሲሊሲያ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር በወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ገመቹ ጎዳና ቀዳሚ ሆኗል።
በርቀቱ የተጠበቀውን የዓለምና የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑን ሞሮኳዊ ሶፍያን ኤል ባካሊን በመብለጥ ነው ያሸነፈው ። ገመቹ ርቀቱን ለመጨረስ 8 ደቂቃ ከ02 ሰከንድ ፈጅቶበታል።
በሴቶች 1500 ሜትርም ምሽቱን ተጠባቂ የነበረው ሩጫ ሲሆን የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ሻምፒዮኗ ፅጌ ድጉማ ስታሸንፍ ርቀቱን ለማጠናቀቅም 3 ደቂቃ 55 ሰከንድ ወስዶባታል።
ብርቄ ኃየሎም 8ኛ ሳሮን በርሄ 11ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
ሌላው የተጠበቀው እና ከ8 በላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተሳተፉበት የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ወድድር የተጠበቀችው ፍሬወይኒ ኃይሉ
በጣሊያናዊቷ ናዲያ ተቀድማ ሁለተኛ ስትሆን ሌሎቹ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአራተኛ እስከ አስራ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
ዳናይት ሲሳይ
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here